ለኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ የ2017 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች ስልጠና መሰጠት ተጀመረ

Training for 2017 graduating students of the College of Informatics has begun.

ለኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ የ2017 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች ስልጠና መሰጠት ተጀመረ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢንፎርማቲክስ ኮሌጅ "ከነርቸር ፕሮጀክት" ጋር በመተባበር ለኮሌጁ የ2017ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎች ከምረቃ በኋላ ላለው ቀጣይ ህይወታቸው አጋዥ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ከዛሬ ሰኔ 27/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 6 ቀናት የሚቆይ ስልጠና በምህንድስና ኢንስቲቲዩት የስልጠና አዳራሽ መሰጠት ተጀምሯል፡፡

በዚህ የስልጠና መርሀ-ግብር የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ወርቁ አበበ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ፣ተመራቂ ተማሪዎቹ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ወስደው 100 % በማለፋቸው የፈጠረላቸውን ደስታ ገልፀው ፣ ለዚህ ውጤት መምጣት በየደረጃው አስተዋፅዖ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል፡፡ ዶ/ር ወርቁ አያይዘውም ስልጠናው ያተኮረባቸውን ርዕሰ ጉዳዮችን በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን፣ "በነርቸር ፕሮጀክት" በኩል የተሰሩ በርካታ ዘርፈ ብዙ ስራዎችንም አቅርበዋል፡፡

"የነርቸር ፕሮጀክት" ዋና አስተባባሪ የሆኑት ፕ/ር ሸጋው በበኩላቸው በበየነ መረብ የተሳተፉ ተመራቂ ተማሪዎች ወደ ስራ ዓለም ከመግባታቸው በፊት አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮች ላይና ለስራ ዝግጁ እንዲሆኑ ከማድረግ አኳያ ብቁ አድርጎ ማውጣት ላይ ፕሮጀክቱ አተኩሮ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡ወደፊትም ከሶስተኛ አመት ተማሪዎች ጀምሮ ለመጀመር መታሰቡንና ይህ ፕሮግራም ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችና ለቀጣይ ፕሮጀክቶች ጥሩ ልምድ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ተናግረዋል፡፡ ቀደም ሲል በፕሮጀክቱ የተከናወኑ ተግባራትና በዓላማው ዙሪያ አጭር ገለፃ አቅርበው ለተመራቂ ተማሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በተመሳሳይ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ"ነርቸር ፕሮጀክት" አስተባባሪ ዶ/ር ዳንኤል ታደሰ በበየነ መረብ የተሳተፉ ተመራቂ ተማሪዎች ባሰመዘገቡት ውጤት መደሰታቸውን ገልፀው፣ ለተገኘው ውጤት በየደረጃው አስተዋፅዖ ያደረገጉ አካላትን አመስግነዋል፡፡

ስልጠናው ተመራቂ ተማሪዎች ወደስራ አለም ሲገቡ በቀጣይ ህይወታቸው ሊሰሯቸው ያቀዱትን አቅድ ማሳካት እንዲችሉ የሚረዱ እውቀት ፣ ክህሎትና አመለካከትን የሚገበዩበት እንደሆነ በመርሀ-ግብሩ የመክፈቻ ንግግራቸው የሚያነሱት የአካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ፣ ተመራቂዎች ቀሪውን የስራ ዓለም ህይወታቸውን ውጤታማና ስኬታማ ለማድረግ ጊዜያቸወን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባቸው አፅንዖት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡

ቀጥሎም በተመረጡ ርዕሶች ስልጠናው እየተሰጠ ይገኛል፡፡

*************************

ለልህቀት እንተጋለን!

የህዝብ ግንኘነት ዳይሬክቶሬት

ሰኔ 27 /2017ዓ/ም

 

What's Your Reaction?

like

dislike

love

funny

angry

sad

wow